በልደታ ክ/ከተማ የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ዋና ዋና አገልግሎቶች
- 1. በቅሬታና አቤቱታ ቡድን የሚሠጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- የቅሬታ አቤቱታ ምርመራ ውሳኔ መስጠት
- መረጃ በጽሁፍ መቀበል
- ከዋና ስራ አስፈጻሚ የተመራ ቅሬታና አቤቱታ ማጣራት፤ መመርመር፤ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፤ ውሳኔ መስጠት፤
- የውሳኔ ሀሳብ ይቅረብልኝ ጥያቄ መቀበልና መልስ መስጠት፤
- በውሳኔው መሰረት ያልፈፀሙ አካላትን መለየት፤
- 2. በወሳኔ አፈጻጸም ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- በጽ/ቤቱ ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን ተከታትሎ እንዲፈጸሙ ክትትል ያደርጋል፣
- ውሳኔ አግንኝው በውሳኔው መሰረት ተፈጻሚ የማያደርጉ ተቋማትን ተጠያቂ ያደርጋል፣
- ተጠያቂ የተደረጉ አካላት ተገቢው የቅጣት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለሚመለከታቸው የፍትህ አካላት መረጃና ማስረጃዎችን አደራጅቶ ይሰጣል
- የጽሁፍ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው ምላሽ የሚያዘገዩና የማይሰጡ ተቋማትን / አካላትን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡
- 3. በመልካም አስተዳደር ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- የመልካም አስተዳደር ችግር ያለባቸውን ተቋማት መለየት
- የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከብሎክ አደረጃጀት ጀምሮ መለየትና መፍታት፤
- የመልካም አስተዳደር ድጋፍና ክትትል ማድረግ ፤
- የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ሱፐርቪዥን ማድረግ፤
- የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን ለማስረጽ ግንዛቤ መፍጠርና ስልጠና መስጠት፤
- የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸምማ ውይይት ማካሄድ፤
- የመልካም አስተዳደር ችግሮች ፣ቅሬታና አቤቱታን ከምንጩ ለመቀነስ በችግሮቹ ዙሪያ ጥናት ማካሄድ፤
- 4. በተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርና ድጋፍ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- የቅንጅት ትስስር ስምምነት ፕሮቶኮል ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤፤
- የተቋማት ቅንጅት ለመፍጠር እቅድ ማዘጋጀት፤
- ተቋማት ተቀናጅተው እንዲሰሩ በማዕቀፉ መሠረት ቅንጅታዊ አሰራር የትስስር ሰነድ እንዲፈራረሙ ማድረግ፤
- የአፈፃፀም ቁልፍ አመላካቾችን በመቅረጽ ክትትል ማድረግ፤
- የቅንጅታዊ አሰራር ክትትል ሪፖርትና ግብረ-መልስ ማዘጋጅትና ማሰራጨት፤
- የቅንጅታዊ አሰራር በየሩብ ዓመቱ ስራዎችን በጋራ መገምገምና ግምገማ ማካሄድ፤
- የቅንጅታዊ አሰራር ትስስር ሰነድ ከተፈራረሙ በኃላ በውላቸው መሸረጽ ያላከናወኑ ተቋማትን ተጠያቂነት ማረጋገጥ፤
- ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማሥፋፋት፤
- ቅንጅታዊ አሰራር እንዲፈጠርና እንዲጠናከር መስራትና ውጤት ማስመዝገብ፤