`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

እንደ አጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየጨመረ የመጣው የህዝብ ቁጥር እና የአገልግሎት ፍላጎት በመንግስት ተቋማት የሚሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶችና ብዛት እንዲጨምር በማድረጉ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ከነዋሪው ሕዝብ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም በየጊዜው አዳዲስ ማሻሻያዎች እየተደረገ ይገኛል፡፡ እንደ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ የጀመረችው የልማት እንቅስቃሴ ከግብ ለማድረስ በርብርብና በጥበብ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን ጽ/ቤታችንም የነዋሪውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለማሳካት አዲሱን ሪፎርም በመተግበር በሰው ህይል አደረጃጀት ፣ በግብአትና በቴክኖሎጂ በመታገዝ የበኩሉን ለመወጣት እየሰራ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤታችን በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ለሙሉ የሰው ሀይል ተሟልቷል ባይባልም ቀጥይ ክፍተቱን ለማሟላት ከከንቲባ ጽ/ቤት መልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ፣ ከፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤትና ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በክ/ከተማም ሆነ በወረዳ ክፍተቱን የሚሟላበትን ጥረት ይደረጋል፡፡

ጽ/ቤታችን የሚከተለው የከተማው አስተዳደር ማቋቋምያ ቻርተር ቁጥር 361/1995 መሠረት ለከንቲባው ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነት አንዱ በአንቀጽ 21/2/ሸ እንደተገለጸው እንደ ክፍለ ከተማ የህዝቡ ቅሬታና አቤቱታ አጣርቶ የመፍታትና ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡ በአዋጅ ቁጥር 71/2014 አስፈጻሚውን አካል እንደገና ለማቋቋም በወጣው አወጅ መሰረት ሀብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳር ችግሮችና እና ቅሬታዎች ተቀብሎ እንዲፈታ በተሰጠው ስልጣን መሰረት እሮብ እና አርብ በአንድ ማእከል በዋና ስራ አስፈጻሚዋ መሪነት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ኃላፊና ባለሙያዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ያለ ሲሆን በመደበኛ የመልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት የሚቀርቡትን ቅሬታዎች በማስተናገድ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል፡፡ እንደ ልደታ መልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ስራዎች በቅንጅት በመስራት የተሻለ ውጤት ይገኝ ዘንድ ተቋማት በቅንጅት በመስራት ቀደም ሲል ይወጣ የነበረውን የሀብት ብክነት በመቀነስ የሚሰጡት አገልግሎቶች የተሳለጠ ለማድረግ በጽ/ቤታችን የሚገኘው የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ቡድን የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡ ይህ የስምምነት ሰነድም የተጀመሩትን የለውጥ ሂደቶችን ቀጣይነት እንዲኖራቸውና ፤የመልካም አስተዳደር አገልግት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም ተቋማችን በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማስፈን እንዲቻል ይህ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ
  2. ተጠያቂነትን በግልጽ ለማመላከት
  3. ዜጎች ምን አይነት አገልግሎት በምን አይነት ጥራት ምን አይነት አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ
  4. ዜጎች በክ/ከተማው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቶአቸው አስተያየትና ጥቆማ እንዲሰጡ ለማሳወቅ
  5. አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ፣
  6. በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ቸግሮችን መፍታት ናቸው፡፡

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች

    የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Mission and Vision ይጫኑ

የጽ/ቤቱ ዋና ዋና አገልግሎቶች

    የጽ/ቤቱ ዋና ዋና አገልግሎቶች ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Our Services ይጫኑ

የተገልጋዮች መብት

  1. ስለ አገልግሎቶች የተሟላ መረጃ የማግኘት፣ የመጠቀምና የሚጠይቀውን ወጭ የማወቅ ብት፣
  2. ተገቢውን አገልግሎት ሳያገኝ ሲቀር ማስተካከያ የመጠየቅ መብት፣
  3. ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት አላቸው፤
  4. በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ጥያቄ የመጠየቅ እና ማብራሪያ የማግኘት መብት፡፡ ፤
  5. ተገልጋዮች አገልግሎቱን ሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያላባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ የማወቅ መብት አላቸው፡፡፤
  6. የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት፣
  7. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያት/ቅሬታ የማቅረብ እና ላቀረቡት ጥያቄ ፍታሃዊ እንዲሁም ወቅታዊና በቂ መልስ የማግኘት መብት፣
  8. ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ የመስተናገድና አግልገሎት የማግኘት መብት፤
  9. በጽ/ቤቱ ዕቅድ፣ ሪፖርትና ግብረ መልስ ላይ መሳተፍና አስተዋጽዖ የማድረግ፡፡ ፤
  10. ፍትሃዊና አድሎ የሌለበት አገልግሎት የማግኘት መብት፤

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. የአገልግሎት ሰጪ ተቋምን ሕጎችን የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
  2. ትክክለኛ መረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ
  3. የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላትና የማቅረብ ግዴታ
  4. የጽ/ቤታችን ህግና ሥርዓት የማክበር ግዴታ

አጠቃላይ የጥራት መርሆዎች

  1. የደንበኛ ፍላጎት ለማርካት እንተጋለን
  2. የሰራተኛውን ሙሉ ተሳትፎ መረጃ ላ የተመሰረተ ውሳኔ ሰጭነት እናዳብራለን
  3. የተቀናጀና ውጤታማ የሆነ የስራ ሂደት ላይ እንመሰረታለን
  4. የአሰራር ስርአት ማሻሻልን ታሳቢ እናደርጋለን
  5. ከባለድርሻ አካላት ጋር መልካም የስራ ግንኙነት እንዲኖር እናደርጋለን
  6. የሰለጠነና የሙያ ብቃት ያለው የሰው ሀይል እንፈጥራለን

የቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርአት

  1. ቅሬታ ያጋጠመው ተገልጋይ በቀጥታ አገልግሎት ለሰጠው ፈጻሚ በቃል ፤በጽሁፍ ፤በስልክ ፤በፋክስና በኢሜል ይሆናል
  2. ቅሬታው የቀረበለት ፈጻሚም የቀረበለትን ቅሬታ አጣርቶ ወዲያውኑ ለቅሬታ አቅራቢው ተገቢውን ምላሽ መስጠት አለበት
  3. በተሰጠው ምላሽ ያልረካ ዜጋ ቀጥሎ ላለው ሀላፊ ቅሬታውን እንዲፈታ ማቅረብ ይችላል
  4. በዚህ ሁኔታ የቀረበለት ሀላፊም ቅሬታውን አጣርቶ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠት አለበት
  5. በዚህ ያልረካ ዜጋ ጉዳዩን ለተቋሙ የበላይ ሀላፊ ማቅረብ ይችላል ፤የበላይ ሀላፊውም ቅሬታው እንዲጣራ በማድረግ ለቅሬታው አቅራቢው መልስ መስጠት አለበት ፤
  6. በመጨረሻ እነዚህን ደረጃዎች ተከትሎ ዜጋው ምላሽ ካላገኘ /አግባብ ባለው ፍርድ ቤት ፤ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቃም ፤ለሰብአዊ መብት ኮምሽን ፤ለሚድያ እና ለስነ ምግባር ጸረ ሙስና ኮምሽን ማቅረብ ይችላል ፡