የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
በመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና ለሚያጋጥም ቅሬታና አቤቱታ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት፣ ስህተቶችን ለማረምና አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ፤ በየደረጃው ያለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊ እና ሠራተኛ ለህብረተሰቡ በሚሰጡት አገልግሎት አስተዳደራዊ ጥፋትና በደል እንዳይፈፀሙ መከላከልና ተፈጽሞ ሲገኝ ተጠያቂ ለማድረግ እና በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ የመስሪያ ቤት ኃላፊና ሠራተኛ በማፍራት ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡
አላማውን መሰረት በማድረግ በክፍለ ከተማችን በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥር እና የአገልግሎት ፍላጎት በመንግስት ተቋማት የሚሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶችና ብዛት እንዲጨምር በማድረጉ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ከነዋሪው ሕዝብ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም በየጊዜው አዳዲስ ማሻሻያዎች እየተደረገ ይገኛል፡፡ ... ተጨማሪ ያንብቡ
አቶ ይልማ ተረፈ , የልደታ መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ኃላፊ


















