image
image
image
image
image

"በክፍለ ከተማው እየተሰጠ ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እየሆነ ነው" ተገልጋዮች

ህዳር 6, 2017
"ከተገልጋዩ ፍላጎት ጋር የሚመጣጠን አገልግሎት ለመስጠት እየሰራን ነው" ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በልደታ ክ/ከተማ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያነጋገራቸው ተገልጋዮች እንደገለፁት በክፍለ ከተማው እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እየሆነ ነው ብለው ለጠየቅነው አገልግሎት የሚሰጠን ምላሽ ተገቢ እና ምልልስን የሚቀንስ ነው በማለት ገልፀዋል። ተገልጋዮች አክለውም በክ/ከተማው እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰረታዊ ለውጥን ያመጣ እና ውጤታማ በመሆኑ ደስተኞች ነን ሲሉ ገልፀዋል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ለማህበረሰቡ የምናቀርበው አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማና የዜጎችን እርካታ ማረጋገጥ እንዲችል ለማድረግ በትኩረት እየሰራን እንገኛለን ብለው በዚህም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ባሉ ተቋማት ውጤታማና ችግር ፈች አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር በቅንጅት እየሰራን ነው ሲሉ ገልፀዋል። እርካታን በማረጋገጥ ተገልጋዮች በተቋማቶቻችን ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ለማስቻል ከምንጊዜውም በላይ በርብርብ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ወ/ሮ ልዕልቲ። ዋና ስራ አስፈፃሚዋ የተገልጋዮችና የተቋማት ግንኙነት በመተማመንና በውጤታማነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ሰፋፊ ስራዎችን እየተከናወኑ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች