image
image
image
image
image

የህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር ለቴክኒክ ኮሚቴዎችና ባለሙያዎች በክላስተሩ ቅንጅታዊ አሰራር ማስፈፀሚያ ማንዋል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::

ታህሳስ 27, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአዲሱ የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር የማስፈፀሚያ ማንዋል ሠነድ ለህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ ፣ለክላስተር አባል ጽ/ቤቶች፣ ለቴክኒክ ኮሚቴዎች እንዲሁም ለሠራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው ስለክላስተሩ አደረጃጀት፣ ስለ ክላስተሩ አስተባባሪ ሚና፣ የክላስተር አባል ጽ/ቤቶች ሚና እና ከቴክኒክ ኮሚቴዎች የሚጠበቅ ሃላፊነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በተጨማሪም በክላስተሩ ዕቅድ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በጥልቀት አንስተው ግንዛቤ ለታዳሚው ፈጥረዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ መፈጠሩን በመግለፅ የክላስተር አባል ጽ/ቤቶች ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ወንጀሎችን፣ የደንብ ጥሰቶችንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን በመከላከል የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ፤ ለህብረተሠቡ እየተሠሩና እየመጡ ያሉ ለውጦችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ በመግለፅ በዕቅዱ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት የጋራ መግባባት ተፈጥሯል::

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች