image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋይ ተኮር በመሆኑ ደስተኞች ነን- ተገልጋዮች

ታህሳስ 24, 2017
በአገልግሎት አሰጣጥ የነበረውን ስብራት እየጠገን የደንበኞችን እርካታ የሚያረጋግጥ ፈጣን ግልፅና ምላሽ ሰጭ አገልግሎት እየሰጠን ነው-ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በልደታ ክ/ከተማ እየተሰጠ የሚገኘው የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በውጤታማነቱ በተገልጋዮች ዘንድ ምገሳ እየተቸረው ነው። ተገልጋዮች እንደገለፁት በአስተዳደሩ እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ችግር ፈች ነው ብለው አገልግሎት አሰጣጡ ተገልጋይ ተኮር እና የተገልጋይ ፍላጋጎትን የሚያሟላ በመሆኑ ደስተኞች ነን ሲሉ ገልፀዋል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም የነበረው የአገልግሎት አሰጣጥ በተገልጋዮች ዘንድ የቅሬታ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል ብለው አሁን ላይ "በአዲስ ዕይታ የልደታ ከፍታ "በሚል መነሻ በአገልግሎት አሰጣጡ የነበሩ ስብራቶችን ጠግነን እርካታን የሚያረጋግጥ ፈጣን ግልፅና ምላሽ ሰጭ አገልግሎት እየሰጠን ነው በማለት ተናግረዋል። ተገልጋዮቻችን የሚያቀርቡትን ጥያቄ በተቀናጀ መንገድ ምላሽ እየሰጠን የልደታን ከፍታ የማረጋገጥ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ። በየደረጃው የሚሰጠው አገልግሎት አሰጣጥ ምልልስን የሚቀንስ እርካታን የሚያረጋግጥ እንዲሆን ለማስቻል ከምንጊዜውም በላይ በትጋትና በቁርጠኝነት እየሰራን ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች